Bid Ethiopia

Bid Ethiopia header image 2

ሆስፒታሉ የተለያዩ የጥገና ዕቃዎች ማለትም የፍሎረሰንት አምፑሎች የተለያዩ፣ መጠን ያላቸው የኤሌክትሪክ ገመዶች፣ ሶኬቶች፣ የበር መክፈቻዎችና እጀታዎች፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው የቧንቧ ዕቃዎችና የመሳሰሉትን እንዲሁም ቋሚ የህክምና መሳሪያዎች፣ ኮምፒዩተሮች፣ ፋይል ካቢኔቶች፣ ወንበሮች እና የጤና ባለሙያዎች የደንብ ልብስ፣ ጫማዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ለሕክምና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ህትመቶችና የፅዳት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

No Comments · Building Materials, Cleaning & Janitorial, Cleaning & Janitorial Equipments, Computer & Accessories, Computer Accessories, Computer Sales, Electrical & Electronic, Electrical Equipment & Accessories, Electronic Equipment & Accessories, Furniture, Health, Health Related Tools & Accessories, Leather Products, Medical Equipments & Supplies, Medical/Laboratory Equipment Maintenance, Office Furniture, Office Items & Equipment, Office Supplies & Stationary, Printing & Publishing, Printing & Publishing Service, Purchase, Textiles & Leather Products, Textiles, Fabrics and Wearing, Water Engineering Machinery, Equipment & Tools

አዲስ ዘመን ዓርብ ጥቅምት 2 ቀን 2005 ዓ.ም

የጨረታ ማስታወቂያ

የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የተለያዩ የጥገና ዕቃዎች ማለትም የፍሎረሰንት አምፑሎች የተለያዩ፣ መጠን ያላቸው የኤሌክትሪክ ገመዶች፣ ሶኬቶች፣ የበር መክፈቻዎችና እጀታዎች፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው የቧንቧ ዕቃዎችና የመሳሰሉትን እንዲሁም ቋሚ የህክምና መሳሪያዎች፣ ኮምፒዩተሮች፣ ፋይል ካቢኔቶች፣ ወንበሮች እና የጤና ባለሙያዎች የደንብ ልብስ፣ ጫማዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ለሕክምና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ህትመቶችና የፅዳት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቸች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

1. ከላይ የተገለጹትን አቅርቦቶች ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በተጨማሪም የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበትንና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ፣ የታክስ ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ ጠቅላላ የመሸጫ ዋጋቸው ከብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ለሆኑት ዕቃዎች አቅራቢዎቹ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይ መሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3. ለጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ከቀረበው ዋጋ 3% በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች ሰነዱን በራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7. የጨረታው ጊዜ የሚያበቃው የስራ ቀን ከሆነ በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡ የሥራ ቀን  ካልሆነ ከአሥረኛው ቀን በኋላ ባለው የሥራ ቀን 11፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡ በአስራ አንደኛው ቀን ወይም የጨረታ ጊዜው ባበቃ በማግስቱ ባለው የስራ ቀን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ የጨረታ ኮሚቴ በሚገኝበት ቢሮ ውስጥ በግልፅ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሆነው ሲቀርቡ ዕቃዎቹን በራሳቸው ማጓጓዣ እስከ ሆስፒታሉ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውንና ፊርማቸውን እንደዚሁም ማህተማቸውን በእያንዳንዱ የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡

10. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

11. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑ ለወደፊቱም በመንግስት እንዳይሳተፉ የሚደረግና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ ይሆናል፡፡

12. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ሁሉ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

13. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ መስሪያ ቤቱ ጨረታው በተከፈተ እስከ አስር የስራ ቀናት ውስጥ ለአሸናፊ ድርጅቶች በፅሁፍ ያሳውቃል፡፡

14. በጨረታ መወዳደሪያ የሚቀርብ ዋጋ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡

15. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ከመስሪያ ቤታችን ጋር ውል ተዋውሎ የውል ማስከበሪያ የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም አሸናፊው ድርጅት ዕቃውን እስከ 15 ቀናት ውስጥ መስሪያ ቤታችን ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ይህ ባይሆን ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ቼክ ወይም ሲፒኦ ለመስሪያ ቤቱ በቀጥታ ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡

16. መስሪያ ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አሰፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች ያቀረበው ዋጋ ሳይቀር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡

17. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ዝርዝራቸው ተጠቅሶ ነገር ግን መለኪያቸውና ብዛታቸው ባዶ ለተደረጉት አቅርቦቶች ዋጋ ማስቀመጥ የለባቸውም፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

በስልክ ቁጥር 0111571563 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል፡፡

Tags:

No Comments so far ↓

There are no comments yet...Kick things off by filling out the form below.

Leave a Comment