Bid Ethiopia

Bid Ethiopia header image 2

ዩኒቨርሲቲው ለICT መሰረተ ልማት የሚውል ሶፍትዌሮች፣ ሀርድዌሮችና ተዛማጅ እቃዎች አቅርቦትና ሥራ፣ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁሶች፣ ቋሚ የህክምና እቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ጥገና እድሳት እቃዎች፣ የውኃ መስመር ዝርጋታ እቃዎች፣ የውኃ ጥራት ላብራቶሪ ቋሚና አላቂ እቃዎች፣ የንጽህና እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

No Comments · Building Materials, Cleaning & Janitorial, Cleaning & Janitorial Equipments, Electrical & Electronic, Electrical Equipment & Accessories, Health, Health Related Tools & Accessories, Laboratory & Chemicals, Laboratory Equipments, Leather Products, Medical Equipments & Supplies, Medical/Laboratory Equipment Maintenance, Networking Tools & Accessories, Office Supplies & Stationary, Purchase, Software, Software & Networking, Sports, Camping & Leisure, Stationery Supplies, Textiles & Leather Products, Textiles, Fabrics and Wearing, Water & Water Works, Water Engineering Machinery, Equipment & Tools

አዲስ ዘመን ቅዳሜ መስከረም 26 ቀን 2005 ዓ.ም

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር ግ/ጨ/02/2005 ዓ.ም

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2005 በጀት ዓመት ለሚያካሂደው የመደበኛ ትምህርት መርሃ ግብር አገልግሎ የሚውሉ ቀጥሎ የተመለከቱትን የቋሚና አላቂ እንዲሁም የሶፍትዌሮችና ሀርድዌሮች ተዛማጅ እቃዎችን በምድብ ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ምድብ 1 ለICT መሰረተ ልማት የሚውል ሶፍትዌሮች፣ ሀርድዌሮችና ተዛማጅ እቃዎች አቅርቦትና ሥራ፣

ምድብ 2 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣

ምድብ 3 የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁሶች፣

ምድብ 4 ቋሚ የህክምና እቃዎች፣

ምድብ 5 የኤሌክትሪክ ጥገና እድሳት እቃዎች፣

ምድብ 6 የውኃ መስመር ዝርጋታ እቃዎች፣

ምድብ 7 የውኃ ጥራት ላብራቶሪ ቋሚና አላቂ እቃዎች፣

ምድብ 8 የንጽህና እቃዎች

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች፡

1ኛ በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ኦርጅናል የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ሊስት /ዝርዝር/ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የምስክር ወረቀትና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ኦርጅናልና የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ባለሥልጣን ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው አካል የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2ኛ ስለጨረታው የሚገልፀውን የሁሉም ምድ የጨረታ ሰነድ የማስገቢያ ቀን ጥቅምት 13 ቀን 2005 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን የሚከፈትበት ቀን ምድብ 1 በጥቅምት 13 ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት እንዲሁም ከምድብ 2 እስከ 8 ጥቅምት 14 ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ለምድብ 1 ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ ለቀሩት ለእያንዳንዱ ምድብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ አዲስ አበባ አሜሪካን ኤምባሲ ፊት ለፊት የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ከሚገኘው የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈፀሚያ የቢሮ ቁጥር 251 ወይንም ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግዢ ን/የሥ/ሂደት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመግዛት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተቋቋሙበትን የህጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለ ክፍያ በነፃ ይሰጣቸዋል፡፡

3ኛ የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ ከምድብ 1 እስከ 8 እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አ.አ በሚገኘው የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ ቁጥር 251 ወይንም አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግዥ ን/የሥ/ሂደት ቢሮ የተዘጋጀ ሳጥን መክተት ይቻላል፡፡ ሰነዱ ታሽጎ ባይቀርብና ተፈላጊ ሰነዶች ቢጎድልበት ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል፡፡

4ኛ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/

ለምድብ 1 Lot 1 ብር 65,000 /ስልሳ አምስት ሺህ ብር/

2 Lot 2 ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/

3 Lot 3 ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/

4 Lot 4 ብር 45,000 /አርባ አምስት ሺህ ብር/

5 Lot 5 ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/

6 Lot 6 ብር 75,000 /ሰባ አምስት ሺህ ብር/

7 Lot 7 ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/

8 Lot 8 ብር 46,000 /አርባ ስድስት ሺህ ብር/

9 Lot 9 ብር 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/

10 Lot 10 ብር 7,000 /ሰባት ሺህ ብር/

ምድብ 2 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ብር 40,000 /አርባ ሺህ ብር/

ምድብ 3 የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁሶች ብር 18,200 /አስራ ስምንት ሺ ሁለት መቶ ብር/

ምድብ 4 ቋሚ የህክምና የእቃዎች ብር 7,180 /ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ብር/

ምድብ 5 የኤሌክትሪክ ጥገናና እድሳት እቃዎ ብር 11,645 /አስራ አንድ ሺህ ስድስት መቶ አርባ አምስት ብር/፣

ምድብ 7 የውኃ ጥራት ላብራቶሪ ቋሚና አላቂ እቃዎች ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/

ምድብ 8 የንጽህና እቃዎች ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ/

በግዥ መመሪያ አንቀጽ 16.16.4 መሰረት ተገቢውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከመጫረቻ ዋጋ ጋር ማቅረብ ሲኖርባቸው ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በጨረተው በተናጠል የሚወዳደሩ አቅራቢዎች የእያንዳዱን ምድ ጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

5 የጨረታው ሳጥን ምድብ 1 ጥቅምት 13 ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት እንዲሁም ከምድብ 2 እስከ 8 በጥቅምት 14 ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋ 4፡30 ሰዓት አዲስ አበባ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግዥ ን/ስ/ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

6 ከምድብ 1 ውጪ ለሚወዳደሩባቸው የዕቃ ዓይነቶች ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቾች በጨረታው አይካፈሉም፡፡

7 የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች ከዩኒቨርሲቲው ጋር ውል በመግባት ማንኛውንም ወጭ በራሳቸው ችለው ለዩኒቨርሲቲው ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋሉ፡፡

8 ተጫራቾች ማንኛውንም የመንግስት ታክስና የግብር ግዴታቸውን ከነመጓጓዣው በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች ከላይ በምድብ የተጠቀሱትን እቃዎችን በከፊል ወይንም በሙሉ በመጫረት መወዳደር ይችላል፡፡

9 ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሱ አድራሻዎች ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ስልክ ቁጥር 0111235224 /አዲስ አበባ/

የስልክ ቁጥር 0468814533 እና 0468811415 /አርባ ምንጭ/

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ

Tags:

No Comments so far ↓

There are no comments yet...Kick things off by filling out the form below.

Leave a Comment