በኩር ሰኞ ጥቅምት 5 ቀን 2005 ዓ.ም
የደን ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል በምዕራብ ጐጃም ዞን በቋሪት ወረዳ በእናንጊያ ሽሜ፣ የድንጃ ጽዬንና ዛንቢት ቀበሌዎች የሚገኘውን የለማ የህዝብ ደን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
1 ለጨረታ የቀረበውን ደን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው ቦታ ድረስ በመሄድ ጨረታው ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ2ዐ ቀናት ማየት ይቻላል፡፡
2 የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ጨረታውን ባወጣው መ/ቤት በመገኘት የማይመለስ 50 /ሃምሳ/ ብር ብቻ ከፍሎ በስራ ቀናት መግዛት ይቻላል፡፡
3 ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የደን አይነት ለመግዛት የሞሉትን ዋጋ 10 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንድ የደን አይነት መቅረብ ይኖርበታል፡፡