አዲስ ዘመን ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2005 ዓ.ም
የጨረታ ቁጥር አ.መ.ኮ.ድ 05/2005
የመክፈቻና መዝጊያ ቀን ማራዘሚያ
አሮሚያ መንገዶች ኮንስትራክሸን ድርጅት የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን፣ ገልባጭ መኪኖችን፣ አነስተኛ የመስክ መኪኖችንና የውኃ ቦቴ መኪኖችን ከአቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ሰኞ መስከረም 28 ቀን 2005 ዓ.ም እና ማክሰኞ መስከረም 29 ቀን 2005 ዓ.ም በወጣው ማስታወቂያ መሰረት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ዕለት ጥቅምት 6 ቀን 2005 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡
ሆኖም ድርጅታችን ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበትን ዕለት እንደሚከተለው እንዲራዘም ስለወሰነ ተጫራቾች በዚሁ መሰረት እንዲጠቀሙ እናስታውቃለን ፡፡
1. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ ልክ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ቀንና ሰዓት አልፎ የሚቀርብ የመወዳደሪያ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም