ቁጥር ይሰ/መስ/1039/15/01
ቀን 28/01/05
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የይስማላ መሠናዶ አጠ/2ኛ ደ/ት/ቤት ያገለገሉ ዘመናቸው ያለፈባቸው መጽሐፎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም በዘርፉ የሚገኝ ድርጅት
1 የዘመኑ የታደሰና ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው
2 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣
3 ተጫራቾች ኮፒና ኦርጅናል ሰነዶች ለይተው በሁለት ፖስታ አሽገው ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር ጨምረው በአንድ ትልቅ ፖስታ በአንድ ላይ በማሸግ የተጫራቹን ወይም የድርጅቱ ስምና አድራሻ በማህተምና ፊርማ ተደርጐ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከሚከፈተበት ቀን በፊት ማስገባት ይኖርበታል፡፡
4 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የዋጋውን 1 ፐርሰንት በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡