አዲስ ዘመን ሰኞ ጥቅምት 5 ቀን 2005 ዓ.ም
የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተለያዩ ተበዳሪዎች በብድር በወሰዱትና ባልከፈሉት ገንዘብ ምክንያት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 98/90 መሠረት በመያዣ የያዘውን ንብረት በሐራጅ ስለሚሸጥ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛወም ሰው በእለቱ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት የንብረቱን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ በማስያዝ መጫረት የሚቻል ሲሆን ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ በሽያጩ ላይ የሚታሰበውን 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምሮ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ሲኖርበት ላላሸነፉት ተጫራች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡ የባንኩን የብድር መስፈርት የሚያሟላ ተጫራች በብድር የመግዛት ጥያቄ ለባንኩ ማቅረብ ይችላል፡፡ ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በሐራጁ አይገደድም፡፡