አዲስ ዘመን ረቡዕ ጥቅምት 7 ቀን 2005 ዓ.ም
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ሸፈራው ተሾመ እና በፍ/ባለዕዳ በወ/ሮ አበራሽ አማከለው መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 131826 ጥር 14 ቀን 2004 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የቤት ቁጥር 1264 በሆነው ቤት ግቢ ውስጥ ቆሞ የሚገኝ የሠ.ቁ 2-02570 አ.አ የሆነ መኪና የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ሆኖ የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡