አዲስ ልሳን ቅዳሜ ጥቅምት 3 ቀን 2005 ዓ.ም
የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽ/ቤት በን/ስ/ላፍቶ፣ በቦሌና በአራዳ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎች በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፣
1 ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150 በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
2 ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ ድረስ ሄደው የቦታዎቹን አጠቃላይ ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
3 ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡