አዲስ ዘመን ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2005 ዓ.ም
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የአሣ/ወ/ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የጽ/መሣሪያ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች የሰው መድኃኒት የእንስሳት መድኃኒቶች እና ኤሌክትሮኒክስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያለውን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የዘመኑን ግብር የክፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
4. የግዥው መጠን ብር 100,000.00 /መቶ ሺ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡