አዲስ ዘመን ዓርብ መስከረም 18 ቀን 2005 ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ
የውሃ አቅርቦት ማጓጓዝን ይመለከታል
የፕሮጀክት 15 ቤቶች ግንባታ ቅ/ጽ/ቤት በቦሌ አራብሳ ሳይት ለሚያስገነባው የጋራ መኖሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የውሃ ቦቴ በዘርፉ በተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡
1 ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዶችን ሰሚት በሚገኘው የአራዳ ቤቶች ግንባታ ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ማስታወቂያው ከወጣበት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
2 ፕሮጀክት ጽ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡ ሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ አለፍ ብሎ የሚገኘው ፕሮጀክት 15 ቤ/ግ/ቅ/ጽ/ቤት