ቁጥር 576/813/05
ቀን 16/01/05
የጨረታ ማስተወቂያ
የጣና ሃይቅ ትራንስፖርት ድርጅት በማንጐ መዝናኛ ውስጥ ለፑል፣ ለጆተኒ፣ ለዳርት፣ እንዲሁም ለሌሎች ተመሣሣይ መጫወቻዎች የሚሆን ቤት በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልግል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
1 በሙያው የዘመኑ ግብር የተከፈለበትና የታደሰ ፍቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2 ቤቱን በአካል ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡
3 የማይመለስ ብር 30.00 /ሠላሳ ብር/ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜ እስከ 6.00 ሰዓት ጨምሮ/ በድርጅቱ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
4 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የአመታዉ ኪራዩን መጠን 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የክፍያ ማዘዣ ሠነድ /ሲ.ፒ.ኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡