አዲስ ዘመን ቅዳሜ ጥቅምት 3 ቀን 2005 ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር PT-08/2005
የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት በአውሮፕላን ከውጭ ሀገር የሚያመጣቸውና የሚልካቸውን መሳሪያዎችና የመለዋወጫ ዕቃዎች የጉምሩክ አስተላላፊነት /ትራንዚተር/ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
1 በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተገቢው እና በመስኩ ህጋዊ የ2004 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የጉምሩክ ባለሥልጣን የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸውን እና የግብር ከፋይነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላችን ትራንዚተሮች ይጋብዛል፡፡
2 ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን ሰነዶች ዋናውንና ኮፒውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡